ዌይ ፕሮቲን

አይብ በሚዘጋጅበት ጊዜ ከቅቤው ከሚለየው ወተት ውስጥ ካለው የውሃ ክፍል የሚዘጋጀው የዌይ (የአጓት) ፕሮቲን፤ በውስጡ በያዛቸው ኤንዛይሞች አማካኝነት የምግብን መፈጨት በማፋጠን ሰውነታችን በቶሎ እንዲጠቀምበት ይረዳል። የዌይ ፕሮቲን በአንድ አገልግሎት 25 ግራም ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን እና 2.6 ግራም ካርቦሃይድሬት አለው። ድካምን ለመቀነስ እና ጡንቻዎችዎን እንደገና ለመገንባት በሚረዱ BCAAs እና L-Glutamine ተፈጥሮዋዊ ኤንዛይሞች አካቶ ይዟል።

አዲስ ወይም ልምድ ያለው አትሌት ይሁኑ፣ የዌይ ፕሮቲን የጡንቻዎን በሚያጎለብቱበት ጊዜ አጠቃላይ ዕለታዊ የፕሮቲን ፍላጎቶን ለማሟላት እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የፕሮቲን ምንጭ በሚፈልጉበት ጊዜ ያለጥርጥር ቀዳሚው ተመራጭ ነው። ይህ ፕሮቲን ሙሉ በሙሉ ከአጓት የተሠራ እንዲሁም ተደጋጋሚ ማጣሪዎችን ያለፈ ሲሆን፣ በጡንቻ ግንባታ ወቅት በአንድ አገልግሎት በአጠቃላይ 25 ግራም ፕሮቲን ያቀርባል።

ለተሻለ ውጤት ስፖርት በሚሰሩበት ወቅት ይጠቀሙት። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ ፕሮቲን መውሰድ ሰውነትዎ በተቻለ ፍጥነት በጡንቻ ሕብረ ሕዋስዎ ውስጥ እንዲዋሃድ ይረዳል። ሰውነትዎ ከእያንዳንዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ በጣም ብዙ ንጥረ ነገሮችን በቀጥታ ወደ ጡንቻዎቾ የሚወስድበት ጠባብ ጊዜ አለው። ለላቀ ውጤት ከስፖርትዎ በኋላ በተቻለ ፍጥነት ፕሮቲንዎን ይውሰዱ።

ethio-fitness-and-nutrition-product-flavor
በቸኮሌት ጣዕም
ethio-fitness-and-nutirition-product-flavour2
በቫኒላ ጣዕም
ethio-fitness-and-nutirition-product-1-facts

ተጨማሪ መረጃዎች

በአንድ ጊዜ የሚወሰድ: 30 ግራም

አንድ  እሽግ ያለው መጠን: 908 እና 2270 ግራም

አጠቃቀም:1 የሾርባ ማንኪያ(32 ግ) የዌይ ፕሮቲን በ250 ሚሊ ቀዝቃዛ ውሃ ይቀላቅሉ። እንደ ምግብ ማሟያ ፣ በየቀኑ 1 ማንኪያ ይውሰዱ። በስልጠና ቀናት ውስጥ ከስልጠናዎ ከ30 ደቂቃዎች በኋላ 1 ማንኪያ ይውሰዱ። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባልሆኑ ቀናት ከእንቅልፉ ሲነቁ እንዲሁ አንድ ማንኪያ ይውሰዱ።

የአለርጂ መረጃ፡ ወተት ፣ እንቁላል ፣ ኦቾሎኒ ፣ ግሉተን ፣ ለውዝ እና አኩሪ አተር በሚመረትበት ተቋም ውስጥ ይመረታል

ማስጠንቀቂያዎች፡ መድሃኒት እየወሰዱ ከሆነ ወይም ማንኛውም የጤና ችግር ካለብዎ ከመጠቀምዎ በፊት ሐኪምዎን ያማክሩ። ይህንን ምርት እንደ አጋዥ ሚዛናዊ አመጋገብ አካል አድርገው ይጠቀሙ እንጂ ለተመጣጣኝ አመጋገብ ምትክ አይደለም። ከሚመከረው ዕለታዊ መጠን አብልጠው አይውሰዱ! ከልጆች ያርቁ!

የማስቀመጫ ሁኔታዎች: በ5-30 °ሴ መካከል በጥብቅ ተዘግቶ ይቀመጥ። ከቀጥታ ሙቀት ፣ እርጥበት እና የፀሐይ ብርሃን ያርቁ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከፈተ በኋላ ምርቱን ከ6 ወር በላይ አይጠቀሙት።

ተያያዥ ምርቶች

ወደ መረጃ ማዕከላችን ይደውሉ

ዘፍመሽ 2ተኛ ፎቅ ፣ መገናኛ፣ አዲስ አበባ